...

የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ዕድሳትና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

ቀን: Mar 27, 2025

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት የህንጻ ዕድሳት እና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡

በኮንትራት ስምምነቱ መሰረት የባለ ስድስት ወለል ህንጻ የዕድሳት ሥራ፣ የባለ ሁለት ወለል ካፍቴሪያ ግንባታ፣ የግቢ ማስዋብ ሥራ፣ የአስፋልት ንጣፍ እና የአጥር ሥራዎችን የሚያጠቃልለው ፕሮጀክት በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሊሉ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቶችን በመጠቀም ግንባታውን በተቀላጠፈ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ጥረት ማደረጉን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

...

ፕሮጀክቱ በጥሩ የግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

ቀን: Mar 21, 2025

የጊዳቦ ሎት 2 የቀኝ ቦይና መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገልል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለፕሮጀክቱ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሀብት አጠቃቀሙን በማሻሻሉና ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ ግንባታው በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ 4,894 ሄክታር መሬትን በመስኖ በማልማት የአካባቢውን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ወደ ከፊል አርብቶ አደርነት በመቀየር የንሮ ሁኔታውን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡ 

ከ63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ የመያዝ እና ከ13ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም ያለው የጊዳቦ ግድብ ሥራ ፕሮጀክት ግንባታው ተጠናቆ ጥር 26 ቀን 2011ዓ.ም መመረቁ ይታወሳል፡፡

...

የልዑክ ቡድን አባላት የካም ሴራሚክንና ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ

ቀን: Mar 17, 2025

በኢፌዲሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት / ጫልቱ ሳኒ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

...

ፕሮጀክቱ በመልካም አፈጻፀም ላይ ይገኛል

ቀን: Mar 15, 2025

በቢሾፍቱ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ  አየር መንገድ ግሩፕ መልሶ ማስፈር  እና  ማቋቋም የባለ 7 ወለል ቅይጥ ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በመልካም አፈጻጸም ላይ

...

ኮርፖሬሽኑ ከካሳ ዲ’አርጊላ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራራመ

ቀን: Mar 15, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የስሪ ዲ ኮንክሪት ህትመት ቴክኖሎጂን ለማስገባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከካሳ ዲ’አርጊላ ጋር ተፈራራመ፡፡

የስምምነቱ ዋና ዓላማ የላቀ ስሪ ዲ ኮንክሪት ህትመት ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ የህንጻ ግንባታ ጥራት፣

...

የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቀቀ

ቀን: Mar 11, 2025

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሲገነባ የነበረው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጤና ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በርክክብ ሂደት ላይ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሸምሱ ዲኖ ገለፁ፡፡
ኢንጂነር ሸምሱ ጤና ማዕከሉ በፍጥነት፣ በከፍተኛ ጥራት፣ በሚጠበቀው መስፈርትና ምሣሌ ሊሆን በሚችል ደረጃ በመገንባቱ የወረዳው አመራሮችና ነዋሪዎች ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ለዚህም ስኬት ጠንካራ የዕቅድ፣ የቅድመ ዝግጅት፣ የክትትል፣ የድጋፍና የቅንጅት ሥራዎች ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወቱ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡