...

የአለም ምህንድስና ቀን እና አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ

ቀን: Mar 10, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር በመተባበር ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እና የአለም ምህንድስና ቀንን አከበሩ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው፣ የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አማኑኤል መኮንን፣ የተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ቢሮ ሃላፊ ሚስ ሶንያ ቫርጋ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር አባላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በእለቱ ሴቶችን በምህንድስና፣ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ሂሳብ መስኮች ስለማብቃት ፣ ርእደ መሬትን የሚቋቋሙ ህንጻዎች ግንባታን በተመለከተ፣ ስለአከባቢ ፣ የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤና ጉዳዮች ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

...

Concrete Roof Tile Factory Begins Trial Production

ቀን: Mar 6, 2025

ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የኢንዱስትሪ መንደር የተተከለው የኮንክሪት ሩፍታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ፡፡
በኮርፖሬሽኑ የኮንክሪት ሩፍታይልስ ማምረቻ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን እስከ 2 ሺህ 500 ሩፍታይሎችን ማምረት ይችላል፡፡

...

የብረት መቁረጫና ማጠፊያ ዎርክሾፕ

ቀን: Mar 4, 2025

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የብረት መቁረጫና ማጠፊያ (Rebar cutting and bending) ዎርክሾፕ በማደራጀት አስፈላጊ የብረት ግብዓቶችን በማዕከል ደረጃ ለፕሮጀክቶች እያቀረበ ይገኛል፡፡

ይህ ዎርክሾፕ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎችና ፕሮጀክቶች በሚያቀርቡት መጠንና ስኬጁል መሰረት ብረትን በመቁረጥ፣ በማጠፍና በሚፈለገው መንገድ በማስተካከል ብረቱ ጥቅም ላይ ወደ ሚውልበት ፕሮጀክት አንዲደርስ እያደረገ ይገኛል፡፡፡

ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ የተቆረጡና የታጠፉ ብረቶች  ከአንድ ማዕከል እንዲቀርቡ መደረጉ የብረት አጠቃቀም እንዲሻሻል፣  ብክነት እንዲቀንስ፣  ፕሮጀክቶች ብረት በመቁረጥና በማጠፍ

...

ፕሮጀክቱ በማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ ይገኛል

ቀን: Feb 28, 2025

ዘርፈ-ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የበርካታ ህንፃዎችን፣ መጋዘኖችን፣ ሼዶችን፣ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን፣ የአጥርና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን ያካተተው ኃይሌ ጋርመንት የግብርና ውጤቶች ገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መገኘቱ ተገለጸ፡፡
ግንባታቸው በመከናወን ላይ ከሚገኘው የማዕከሉ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ውጭ ሌሎች ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የተገለጸ ሲሆን የተጠቀሱት ቀሪ ሥራዎች በቀርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ፡፡

...

የኮርፖሬሽኑ የግማሽ አመት አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

ቀን: Feb 27, 2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) 6 ወራት አፈፃፃም ገምግሟል።

 

ኮርፖሬሽኑ በእቅድ አፈጻጸሙ  የተሻለ አቋም ላይ እንደሚገኝ  የገለጸው ሆልዲንጉ  በተለይም በመሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም አመላክቷል፡፡

 

ኮርፖሬሽኑ ካለው አቅም አንጻር በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም እንደሚያስመዘግብ ያለውን እምነት በመግለፅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

...

እንኳን ደስ አላችሁ!

ቀን: Feb 15, 2025

ላለፉት ሁለት ዓመታት በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ግንባታው የዘገየው በኢ.ኮ.ሥ.ኮ እየተገነባ የነበረው የያቤሎ ከተማ ባይፓስ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ የክልሉ መንግስት ችግሩን መፍታቱን ተከትሎ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡