የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር
- በዚህ አዋጅ አንቀፅ 11መሰረት ለተቆጣጣሪው ባለስልጣን መቅረብ ከሚገባቸው በስተቀር ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮችን ይወስናል፣
- የድርጅቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይቀጥራል፤ ደሞዝና አበሉን ይወስናል፤ያሰናብታል፣
- ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪጅ ተጠሪ ሆኑ የሥራ ሃላፊዎችን ቅጥር፣ ምደባ እና ስንብት፣ ደሞዝና አበል ያጸድቃል፤
- የድርጅቱን የሥራ ፕሮግራም፣ በጀትና የውስጥ ደንብ ያፀድቃል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
- የድርጅቱን የረጅም ጊዜ ብድሮችና ክሬዲቶች ያፀድቃል፤
- በድርጅቱ ህልውና ላይ ወሳኝነት የሌላቸውን ቋሚ ንብረቶች ሽያጭ ያፀድቃል፤
- የድርጅቱ ሂሳቦችና ንብረቶች በአግባቡ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤
- ለድርጅቱ ኦዲተሮች የድርጅቱን የሂሳብ መዝገቦችለተቆጣጣሪው ባለስልጣን ደግሞ ስለ ድርጅቱ ስራ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርትና የሂሳብ መግለጫዎችን ያቀርባል፤
- የድርጅቱ ካፒታል እንዲጨምርወይም እንዲቀንስ ለተቆጣጣሪው ባለስልጣን ሐሳብ ያቀርባል፡፡