አዳዲስ ዜናዎች

...
ኮርፖሬሽኑ እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በኮርፖሬሽኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች እና ኢንዱስትሪዎች  ላይ የአካባቢ ጥበቃን እና  ዘላቂ  አረንጓዴ ልማት ለማከናወን የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

‎የመግባቢያ ስምምነቱን  የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው  እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ  ተፈራርመዋል።

‎የባለስልጣኑ የማኔጅመንት አባላት  ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ኢንዱስትሪ  ዞን  የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ባካሄደው  ሪፎርም እና  የልህቀት ስትራቴጂ ትግበራ  መደነቃቸውን ገልጸዋል።

Oct 8, 2025
...
ኮርፖሬሽኑና ኢንስቲትዩቱ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) እና የፌደራል ሕግና ፍትህ ኢንስቲትዩት በህግና ፍትህ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ጳጉሜን 03 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው የፊርማ ፕሮግራም ላይ በመገኘት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ደግፌ ቡላ ሰነዱን በፊርማቸው አጽድቀውታል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ኮርፖሬሽኑ እና ኢንስቲትዩቱ በህግና ፍትህ ምርምርና ስልጠና፣ መረጃ መጋራት፣ በኮንትራት ሰነድ ዝግጅት እና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ያስችላቸዋል፡፡
በክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ የተመራው የኢንስቲትዩቱ ልዑካን ቡድን የኮርፖሬሽኑን የኢንዱስትሪ ዞን የጎበኘ ሲሆን ጎብኚዎቹ ኮርፖሬሽኑ እያካሄደ ባለው የሪፎርም ፕሮግራም መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

Sep 10, 2025
...
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግንባታ ፕሮጀክት ተመረቀ

ግንባታው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ) የተከናወነው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግንባታ ፕሮጀክት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል  ብርሃኑ ጁላ  በተገኙበት ተመረቀ፡፡

‎በምረቃ ስነ-ስርአቱ ሌተናንት ጄነራል ሹማ አብደታ የልዩ ዘመቻዎች እዝ  ዋና አዛዥ፣  ሌተናንት  ጄነራል ደስታ አብቼ የመከላከያ መሀንዲስ  ዋና መምሪያ  ሃላፊ፣  የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ  አያሌው  እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች  እንዲሁም የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

‎ከ1.44 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የኮንትራት ዋጋ ግንባታው የተከናወነው ይህ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮጀክት ሦስት (G+4) ህንጻዎች፣ ሦስት (G+2) ዶርሚተሪዎች፣ ስድስት መጋዝኖች፣ አንድ (G+1) ካፍቴሪያ፣ አንድ (G+1) የጤና ማዕከል፣ አንድ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሚታ ያለው መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የነዳጅ ማደያ፣ የኃይል ማመንጫ ክፍል፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታ እና የሰልፍ ቦታ ግባታዎችን፣ የዋና መግቢያ በር እና የአጥር ሥራዎችን ይዟል፡፡

Sep 10, 2025
...
በጋራ አሳክተነዋል

በሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመሪነት ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን አጠናቆ ለምረቃ በማብቃቱ የፕሮጀክቱን ባለቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን እና የቦረና ዞንን እንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ ክላሲክ ኮንሳልቲንግ  ኢንጂነርስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን  እና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።

‎ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ሰርቶ ለማጠናቀቅ ባደረገው ርብርብ አጋጥመው የነበሩትን የወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች በመፍታት ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የቦረና ዞን እንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ ያደረጉት ድጋፍ የሚደነቅ እና ሌሎችም ከዚህ ሊማሩበት የሚገባ ነው።

‎'በጋራ የመስራት' እሴት ውጤታማነትን በጉልህ የሚያሳየው ይህ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለምረቃ እንዲበቃ ሌት ተቀን በመሥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን እና የቦረና ዞንን እንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ ክላሲክ ኮንሳልቲንግ  ኢንጂነርስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንኳን ደስ አላችሁ።
‎ 
‎የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚንስትር አቶ አህመድ ሺዴ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ተገኝተዋል።

‎እናመሰግናለን!

‎የተሻለ ነገን እንገነባለን!

Sep 10, 2025
...
ኮርፖሬሽኑ በ60 ኛው የማፑቶ የንግድ ትርዒት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሩዋንዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ60 ኛው የማፑቶ የንግድ ትርዒት ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

በማፑቶ ኢንተርናሽናል የንግድ ትርዒቱ ኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዘርፈብዙ የሆኑ የሪልሰቴት ልማት ሥራዎችን፣ የግብዓት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎቶችን፣ የዲጅታላይዜሽን ሪፎርም ፕሮግራምን እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሽርክና እየሰሩ ያሉ ኩባያዎች የሥራ እንቅስቃሴዎችን አሳይቷል፡፡

ከነሀሴ 19 ቀን 2017ዓ.ም በሞዛምቢክ ሪካትላ ኤግዚቢሽን ማዕከል የተጀመረው የንግድ ትርዒት እስከ ነሀሴ 25 2017ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ27 አገሮች የተውጣጡ  ከ3ሺህ በላይ የሆኑ ተቋማት በኤግዚቢሽኑ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

Aug 28, 2025
...
ኮርፖሬሽኑ በበጀት አመቱ የላቀ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ካለፉት ዓመታት በተሻለና ከእቅድ በላይ ማሳካቱን 2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ቀርቦ ወይይት ተጨማሪ ያንብቡ

Aug 28, 2025

Latest project

Dima - Rad Road Construction Project

Water sector / completed ____Date:Dec 9, 2022

Dima - Rad the road construction project, 60 km long, is located in Gambella National Regional State. The contractual agreement is signed on January 16, 2015, with the contract amount of Birr 874,442,881. Ethiopian Construction Design and Supervision Works Corporation is the supervisor of the project. The project is completed this year, 2020. It connects Ethiopia with south Sudan

Dima - Rad the road construction project, 60 km long, is located in Gambella National Regional State. The contractual agreement is signed on January 16, 2015, with the contract amount of Birr 874,442,881. Ethiopian Construction Design and Supervision Works Corporation is the supervisor of the project. The project is completed this year, 2020. It connects Ethiopia with south Sudan

Kuraz Irrigation Development Project

Transport sector / completed ____Date:Dec 9, 2022

The Kuraz Irrigation Development Project, which is launched in South N.N.P State at a cost of 417.7.2 million ETB, was begun in Dec 2008 E.C and completed in Aug 2010 E.C.
Successfully subscribe !
Already subscribe with this email !