...

ኮርፖሬሽኑ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር  በመተባበር የቢዝነስ ፎረም አዘጋጀ

ቀን: May 14, 2023

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአፍሪካ ሃገራት መካከል የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማሳደግ የሚያግዝ የምክክር መድረክ ስኬታማ በሆነ መልኩ አካሄደ፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንደተናገሩት በአፍሪካ ሃገራት መካከል ዘርፈ-ብዙ የትብብር ማዕቀፍ ለመመስረት የምክክር መድረኩ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑን የማኔጅመንት ቦርድ በሰብሳቢነት የሚመሩት ኢንጂነሯ እንደተናገሩት በአፍሪካ ከመሰረተ ልማት አውታር ግንባታ አንጻር አፍሪካ ያላትን የታመቀ የገበያ ዕድል ለመጠቀም ሀገራት በዓቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በልምድ ልውውጥ ዘርፎች በጋራ መስራት ይገባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአፍሪካን ሁለንተናዊ ለውጥ ዕውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ወንድምና እህት ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት ከማንኛውም ጊዜ በላቀ ደረጃ ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን እንደተመሰረተ የተናገሩት ሚኒስትሯ ተቋሙ ወደ ፊት ምህንድስና ዲዛይንን፣ የፕሮጀክት ሥራ አመራርን እና ፕሮጀክት አተገባበርን በሚመለከት የምክክር መድረኩን በሚገባ ሊጠቀምበት ይገባል ብለዋል፡፡
የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ኮርፖሬሽኑን በሚመለከት ለምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በሦስት የግንባታ ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመው ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና በውጭ ሀገር ከ100 በላይ የግንባታ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ከ20 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተቋሙ ከግንባታ ሥራዎች በተጨማሪ በፕሮጀክት ዲዛይንና ሥራ አመራር አገልግሎት፣ በግንባታ ግብዓት ማምረትና በግንባታ ላይ በሚያተኩሩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ 
ኮርፖሬሽኑ የአፍሪካ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን በመገንባት ረገድ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር በሽርክናም ሆነ በሌሎች አማራጮች  በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አለው ብለዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የአፍሪካ የኢንጂነሮች ድርጅቶች ፌደሬሽን ፕሬዚደንት ዶክተር ካዛዋንዲ ፓፒያስ ደደኪን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ከቡሩንዲ፣ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ከቻድ፣ ከኡጋንዳ፣ ከጂቢቲ፣ ከኢኩዋቶሪያል ጊኒ እና ከታንዛንያ ኢምባሲዎች የተወከሉ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፡፡              

 

...

የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

ቀን: May 14, 2023

የዚምባቡዌ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብዓት ማምረቻ ማዕከልን፣ በተገጣጣሚ ህንፃ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታንና በቅርቡ የተጠናቀቀውን የኮንስትራክሽን ሙያተኞች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንዳሉት ኮርፖሬሽኑ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የገበያ አድማሱን ለማስፋት በርካታ ሥራዎችን በሚሰራበትና የኢንተርናሽናሌይዜሽን ሪፎርምን ተግባራዊ እያደረግንበት ባለበት ወቅት የተደረገ የልምድ ልውውጥ ስለሆነ ጠቃሚ ልምዶችን የልዑክ ቡድኑ ከኮርፖሬሽኑ እንደሚያገኝ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ግድቦች፣ የመስኖ እና የውሀ አቅርቦት ሥራዎችን፣ የህንፃና ቤቶች ግንባታዎችን በማከናወን ትልቅ ልምድ ያለው ኩባንያ ስለሆነ የነበሩ ልምዶቻችንን እያጎለበትን በጋራ አፍሪካን እንደምንገነባ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡
ከጉብኝቱ በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና ተልዕኮውን የሚያሳይ የ10 ደቂቃ ፕሮሞሽናል ዶክሜንታሪና የኮርፖሬሽኑን የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓት ልዑካን በድኑ እንዲመለከቱ ተደርጓል፡፡
በዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት እና ካቢኔ ጽህፈት ቤት የፖሊሲ ትንተና፣ ማስተባበር እና የልማት እቅድ ምክትል ዋና ጸሃፊ ሚስተር ሚላርድ ማኑንጎ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ የተገጣጣሚ ህንፃ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ እየሰራቸው ባሉ ሥራዎች፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓቱን ቀልጣፋና የመረጃ ልውዉጡን ፈጣን ለማድረግና የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ አምርቶ ለመጠቀም እያደረገው ያለውን ጥረት አድንቀው በቀጣይ በጋራ ከኮርፖሬሽኑ ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡

 

...

Djibouti company officials visit the corporation.

ቀን: May 14, 2023

የጂቡቲ ወደቦች ኮርደርን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን የሚያስተዳድረው “DPCR” የተባለው ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጉብኝት አደርጉ፡፡
ጂቡቲ ውስጥ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካይነት የሚከናወነው የሞሉድ-ዲክሂል-ጋላሞ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት ባለቤት የሆነው የ“DPCR” ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች የኮርፖሬሽኑን የግብዓት ማምረቻ ማዕከል (የጂብሰም ቦርድ፣ የአልሚኒየም፣ የፍሌክሲ ፍሉ፣ የፕሪፋም፣ የታይልስ፣ የተገጣጣሚ ህንፃ አካላት ማምረቻን)፣ በተገጣጣሚ ህንፃ አካላት ምርቶች እየተከናወነ የሚገኘውን የ5 ሺህ ቤቶች ግንባታን እና የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ተወዳዳሪነቱን የሚያሳድጉ ሥራዎችን በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ በማከናወን የኢንተርናሽናላይዜሽን ሪፎርሙን እውን ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ጉብኝቱ በተከናወነበት ዕለት በፕሮጀክት ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ማዕከል ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አርጋው አሻ በኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ፣ በተገኙ ውጤቶች፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት አስተዳደርና አተገባበር፣ በኢንተርናሽናላይዜሽን ሪፎርምና በትኩረት መስኮች ዙሪያ እንዲሁም በኢትዮ-ጂቡቲ ግንኙነት ላይ ለ“DPCR” ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም በዕለቱ በሞሉድ-ዲክሂል-ጋላሞ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጂኦ ቴክኒካል አማካሪ የሆኑት ኢንጂነር አየነው ይሁኔ እና የሐይዌይ ኢንጂነርና የትራንስፖርት አማካሪ የሆኑት ኢንጂነር ሳሙኤል በመንገዱ የዲዛይን ሥራ ላይ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል፡፡ በተለይም በጂኦቴክኒካል፣ በኃይድሮሎጂ፣ በአርክቴክቸራል፣ በስትራክቸራል ዲዛይንና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የ“DPCR” ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎችም ዲዛይኑን የተመለከተው ሪፖርት በጥሩ ሁኔታ በዝርዝርና በጥልቀት የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምክክር በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት እየተወያዩ እንዲሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ ፡በውይይቱ ውቅት የተገኙትና በፕሮጀክት ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ማዕከል የዲዛይን ዲፓርትመንት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ባይሳ መቃ እንዳሉት ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ በማዕከሉ የተዘጋጀው የ10 ኪሎ ሜትር ዲዛይን ተገምግሞ እንዲፀድቅ ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ለመግባትና ቀሪ የዲዛይን ሥራዎችን ለመስራት የ“DPCR” ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ያደረጉት ጉብኝት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ 

የሞሉድ-ዲክሂል-ጋላሞ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በታሰበው መልኩ በማከናወን ወደ ምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ገበያ በስፋት ለመግባት የተሻለ ዕድል እንደሚፈጠርም እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ 45 ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና በ43 ሚሊዮን የአሜረካ ዶላር የኮንትራት ዋጋ የሚከናወን የዲዛይንና የግንባታን ሥራን በአንድ ላይ የያዘ ፕሮጀክት መሆኑን የሞሉድ-ዲክሂል-ጋላሞ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከኢንጂነር ኃይሉ ድንቅነህ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

...

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በ20.3 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታል ተቋቋመ

ቀን: Dec 30, 2022

H.E Mrs. Chaltu Sani, minister of urban and construction of Ethiopia made remarkable speech in the event of women in construction summit in Dubai that, the government of Ethiopia's due attention given for women that 36 percent of the cabinets are females.

The minister also stressed that, there is a need to create conducive policies and procedure to support and attract women in the construction sector. In addition, H.E Mrs. Chaltu Sani remarks that, creation of equal opportunity and realization conducive working environment would also help to promote women's participation in the construction industry.

...

H.E Mrs. Chaltu Sani visits ECWC’s booth at Dubai

ቀን: Dec 29, 2022

Minister of the FDRE Minister of Urban and Infrastructure H.E Mrs. Chaltu Sani, State Minister H.E Mr. Wondimu Seta and State Minister H.E Mrs. Helen Debebe from the same Ministry visited the Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) stand at Dubai World Trade Center opened in December 5, 2022.

H.E Mrs. Chaltu Sani appreciated ECWC’s effort to promote Ethiopia’s investment potential in general and showcasing the Corporation’s effort to attract potential investors to work together to grasp the Eastern and Central African Markets. Furthermore, H.E admired ECWC’s participation in the Global Construction Leaders’ Summit that enables ECWC to gain and share experiences of the state of the art construction project management skills and technologies.

The BIG 5 international building and construction show will be closed in December 8, 2022.

...

ECWC signs an MoU with ACI

ቀን: Dec 29, 2022

The Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) signs an MoU with an American Concrete Institute(ACI) to increase collaboration and cooperation in matters of improving concrete construction through the support of technical expertise in ways of publications, meetings, conferences, internet links, committee membership, and certification activities.

The agreement was signed between Engineer Yonas Ayalew, CEO of ECWC and Charles Nmai , president of ACI in the 7th of December 2022 at Dubai, World Trade Center.